ወላይታ ድቻ ሦስተኛ የውድድር ዘመኑ ፎርፌ አግኝቷል


የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታዎች ከ4:00 ጀምሮ መደረግ ሲጀምሩ ቅዱስ ጊዮርጊስ ለጨዋታ ባለመቅረቡ ወላይታ ድቻ በፎርፌ አሸናፊ ሆኗል።

በአዲስ አበባ ስታድየም የተደረገው መርሐ ግብር ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሊጉ ራሱን ለማግለል በወሰደው ውሳኔ በመፅናቱ ምክንያት ሳይገኝ ሲቀር ወላይታ ድቻ በሜዳ በመገኘት ለ30 ደቂቃዎች ከጠበቀ በኋላ ፈዴራል ዳኛ ኃይለየሱስ ባዘዘው የጨዋታውን ፎርፌ የሚያበስር ፊሽካ አሰምተው ከሜዳ ወጥተዋል።

በዘንድሮው ፕሪምየር ሊግ እስካሁን አራት የፎርፌ ውጤቶች ሲመዘገቡ ወላይታ ድቻ ለሦስተኛ ጊዜ ሦስት ነጥብ እና ሦስት ጎል ማግኘት ችሏል። ቅዱስ ጊዮርጊስም ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ ፎርፌ በመስጠቱ በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን መመርያ መሠረት ከፕሪምየር ሊጉ ውጪ የሚሆን ይሆናል።

በዚህ ሰዓት እየተደረገ በሚገኝ ሌላ ጨዋታ ሀዋሳ ላይ ሀዋሳ ከተማ ከ ደደቢት የመጀመርያ አጋማሽ 2-2 አጠናቀዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡