ቻን 2016 : አንጎላ በዛምቢያ ተሸነፈች

 

በአፍሪካ ሃገራት ዋንጫ (ቻን) በምድብ ሁለት ከኢትዮጵያ፣ ካሜሮን እና ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ የተደለደለችው ደቡብ አፍሪካዊቷ ሃገር አንጎላ ዕሁድ ጁሃንስበርግ ላይ በተደረገ የአቋም መለኪያ ጨዋታ በዛምቢያ 2-1 ተሸንፋለች፡፡ አንጎላ በአድሪያኖ ግብ መምራት ብትችልም ዛምቢያ በክሌተስ ቻማ እና ሙዊላ ፒሪ ታግዛ ማሸነፍ ችላለች፡፡

አንጎላ ባሳለፍነው ዕረቡ ከናይጄሪያ ጋር በፕሪቶሪያ 1-1 ተለያይታለች፡፡ ባርቶሎሚዬ ኤቤንጉቡ በ84ኛው ደቂቃ በፍፁም ቅጣት ምት ግብ ያስቆጠረ ሲሆን አንጎላዎች የአቻነቷን ግብ ማንጉኢ በግንባሩ ገጭቶ አስገኝቷል፡፡

አንጎላ የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋን ከካሜሮን ጋር ታደርጋለች፡፡ አንጎላ በ2011 ሱዳን ላይ በተካሄደው ሁለተኛው የቻን ዋንጫ ላይ በቱኒዚያ ተሸንፋ የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ ነበረች፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *