አፍሪካ ዋንጫ | በዓምላክ ተሰማ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ይዳኛል

የ2019 አፍሪካ ዋንጫ ወደ ወሳኝ ምዕራፍ ሲሸጋገር የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች እሁድ ይካሄዳሉ። ኢትዮጵያዊው በዓምላክ ተሰማም በውድድሩ አራተኛ ጨዋታውን ይመራል።

ከሁለቱ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች መካከል ምሽት 1:00 ላይ በጁላይ 30 ስታድየም የሚካሄደው የቱኒዚያ እና ሴኔጋል ጨዋታ በበዓምላክ ተሰማ የሚመራ ሲሆን ትላንት በሩብ ፍፃሜው አብረውት የዳኙት ሱዳናዊው ዋሊድ አህመድ እና የኮንጎው ኦሊቨር ሳፋሪ በረዳትነት በድጋሚ የሚያጫውቱ ይሆናል።

በዓምላክ በዘንድሮው ውድድር እስካሁን ሦስት ጨዋታዎች የመራ ሲሆን በምድብ ጨዋታዎች ቱኒዚያ ከ አንጎላ እና ጋና ከ ካሜሩን፣ በሩብ ፍፃሜው ደግሞ አይቮሪኮስት ከአልጄርያ ያደረጉትን ጨዋታ መርቶ በድምሩ 11 ቢጫ ካርዶች እና ሁለት የፍፁም ቅጣት ምት ውሳኔዎችን አሳልፏል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡