ቻን 2020 | ኢትዮጵያ የቅድመ ማጣርያ ጨዋታዋን የምታደርግበት ሜዳ ታውቋል

የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) በ2020 ካሜሩን ላይ ይስተናገዳል፡፡ ለዚሁ ውድድር በቅድመ ማጣሪያው ከጅቡቲ ጋር የተደለደለችው ኢትዮጵያ ሐምሌ 19 ጅብቲ ላይ የመጀመሪያ ጨዋታዋን ስታደርግ በሳምንቱ የመልሱን ጨዋታ ድሬደዋ ከተማ ላይ የምታደርግ መሆኑ ታውቋል፡፡

አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ እና ረዳቶቹ በቅርቡ 23 ተጫዋቾች ያሳወቁ ሲሆን ዝግጅታቸውንም ከማክሰኞ ጀምሮ የመልሱን ጨዋታ በሚያደርጉበት ድሬዳዋ ከተማ የሚያደርጉ ይሆናል።

ኢትዮጵያ የመጀመርያ የማጣርያ ጨዋታዋን በድል የምታጠናቅቅ ከሆነ መስከረም ወር ላይ ከሩዋንዳ ጋር የምትጫወት ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡