የአንደኛ ሊግ የማጠቃለያ ውድድር ድልድል ይፋ ሆነ

የ2011 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ የማጠቃለያ ውድድር የምድብ ድልድል ዛሬ በባቱ ከተማ ይፋ ሆኗል።

ከአንደኛ ሊግ ወደ ከፍተኛ ሊግ የሚገቡ ስድስት ክለቦችን የሚለየው የማጠቃለያ ጨዋታ ነገ በባቱ (ዝዋይ) ከተማ ውድድሩ የሚጀምር ይሆናል። ዛሬ የፌዴሬሽን ተወካይ እና የክለብ አመራሮች በተገኙበትም የዕጣ ማውጣት ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል። በዚህም መሠረት

ምድብ 1
ኮልፌ ቀራኒዮ
ላስታ ላሊበላ
ቢሾፍቱ ከተማ
ጎፋ ባሬንቼ
አዲስ አበባ ፖሊስ

ምድብ 2
መቱ ከተማ
ዳሞት ከተማ
ቂርቆስ ክ/ከተማ
ጋሞ ጨንቻ
ራያ አዘቦ

ምድብ 3
ሱሉልታ ከተማ
ባቱ ከተማ
ናኖ ሁርቡ
ቡሌ ሆራ

ምድብ 4
የጁ ፍሬ ወልዲያ
መተሐራ ስኳር
ሶሎዳ ዓድዋ
ሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን

የነገ ሐምሌ 7 ጨዋታዎች

04:00 ቢሸፍቱ ከተማ ከ ጎፋ ባሬንቼ (ባቱ ሜዳ)
07:00 ላስታ ላሊበላ ከ አዲስ አበባ ፖሊስ ( ባቱ ሜዳ)

04:00 ዳሞት ከተማ ከ ራያ አዘቦ (ሼር ሜዳ)
07:00 ኮልፌ ቀራንዮ ከ ጋሞ ጨንቻ (ሼር ሜዳ)


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡