የፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ነገ ይሰበሰባል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ነገ ስብሰባ ሲያደርጉ ለየት ያለ ውሳኔም እንደሚኖርም ይጠበቃል፡፡

የኢትዮጵያ እግርኳስ እና የሀገሪቱ ትልቁ ሊግ ካለፉት ዓመታት በባሰ መልኩ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኝ እንደመሆኑ የወደፊት እጣፈንታው ምን ይሆናል፤ ወደ መልካም ጎዳና ለማምጣትስ ከፌዴሬሽኑ ምን ዓይነት ወሳኔዎች ይኖራሉ? የሚለው የብዙሀን ጥያቄ ነው።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ዛሬ በተለያዩ ጉዳዮች ዙርያ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተገኙት የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ ነገ ፌዴሬሽኑ ስብሰባ እንደሚቀመጥ ተናግረዋል። ” ነገ ከሰዓት የምናደርገው ስብሰባ ጠንከር ያሉ ውሳኔዎች የሚተላለፉበት ነው። ይህንን አስመልክቶም ወደፊት መግለጫ የምንሰጥ ይሆናል።” ብለዋል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡