ኢትዮጵያ ማዳጋስካርን በመግጠም የ2021 አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጉዞዋን ትጀምራለች

በካሜሩን አስተናጋጅነት ለሚከናወነው የ2021 አፍሪካ ዋንጫ የማጣርያ ጨዋታዎች የምድብ ድልድል ባለፈው ሳምንት መውጣቱ የሚታወስ ሲሆን የጨዋታ መርሐ ግብርም ታውቋል።

በምድብ 11 ከአይቮሪኮስት፣ ኒጀር እና ማዳጋስካር ጋር የተደለደሉት ዋሊያዎቹ የማጣርያ ጉዟቸውን ወደ አንታናናሪቮ በማቅናት የሚጀምሩ ሲሆን በሁለተኛ ጨዋታ አይቮሪኮስትን በሜዳቸው ይገጥማሉ። በ2012 ክረምት ሁለት ጨዋታዎች ከሜዳቸው ውጪ እና በሜዳቸው ካከናወኑ በኋላ በ2013 መስከረም እና ጥቅምት ወራት የመጨረሻ ሁለት የማጣርያ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ።

የምድብ 11 መርሐ ግብር ይህንን ይመስላል

ከጥቅምት 29- ህዳር 1 ቀን 2012
አይቮሪኮስት ከ ኒጀር
ማዳጋስካር ከ ኢትዮጵያ

ኅዳር 8-10 ቀን 2012
ኢትዮጵያ ከ አይቮሪኮስት
ኒጀር ከ ማዳጋስካር

ነሐሴ 25-26 ቀን 2012
አይቮሪኮስት ከ ማዳጋስካር
ኒጀር ከ ኢትዮጵያ

ጳጉሜ 2-4 ቀን 2012
ማዳጋስካር ከ አይቮሪኮስት
ኢትዮጵያ ከ ኒጀር

መስከረም 24-26 ቀን 2013
ኒጀር ከ አይቮሪኮስት
ኢትዮጵያ ከ ማዳጋስካር

ጥቅምት 30 ቀን 2013
አይቮሪኮስት ከ ኢትዮጵያ
ማዳጋስካር ከ ኒጀር


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡