ኢትዮጵያውያን ዳኞች የቻን ማጣርያ ጨዋታን ይመራሉ

በካሜሩን አስተናጋጅነት በ2020 ለሚደረገው የቻን ውድድር የማጣሪያ ጨዋታዎች በዚህ ሳምንት ሲጀመሩ አራት ኢትዮጵያዊያን ዳኞች የሶማሊያ እና ዩጋንዳን ጨዋታ ይመራሉ፡፡

የፊታችን ቅዳሜ ሐምሌ 20 ሀገሯ ላይ ጨዋታ ማድረግ ያልቻለችው ሱማሊያ በቅድመ ማጣሪያው ጅቡቲ ላይ ዩጋንዳን ስታስተናግድ አራት ኢትዮጵያዊያን በዳኝነት ይመሩታል። በላይ ታደሰ በዋና ዳኝነት ሲመራው ትግል ግዛው እና ክንፈ ይልማ የበላይ ረዳቶች ናቸው። በአራተኛ ዳኝነት ደግሞ ለሚ ንጉሴ እንደተመደበ ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡

ኢንተርናሽናል ዳኛ በላይ ታደሰ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በርካታ የሊግ ጨዋታዎችን ከመሩ ዳኞች መካከል አንዱ ሲሆን ይህ ፍልሚያ በጥር ወር በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ዜስኮ ከካይዘር ቺፍስ ከዜስኮ ዩናይትድ ጨዋታን ከመራ በኋላ በአፍሪካ የሚመራው ጨዋታ ነው።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡