የእንየው ካሳሁን ማረፍያ የዐፄዎቹ ቤት ሆኗል

እንየው ካሳሁን የፋሲል ከነማ የመጀመርያ ፈራሚ በመሆን ለዝግጅት ወደ ባህርዳር አቅንቶ ቡድኑን ተቀላቅሏል።

ያለፉትን ሁለት ዓመታት በወልዋሎ ጥሩ ቆይታ የነበረው ተጫዋቹ ሊጉ ካለቀ በኋላ ከተለያዩ የሊጉ ትላልቅ ክለቦች ጋር ስሙ እየተነሳ ቢቆይም በመጨረሻም ለቀጣይ የአፍሪካ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ በስፋት በዝውውሩ እንደሚሳተፉ የሚጠበቁት ፋሲል ከነማዎች ማረፍያውን አድርጓል።

ለፌዴራል ፖሊስ ፣ አዲስ አበባ ከተማ እና ወልዋሎ የተጫወተው ይህ ተጫዋች በዚህ ዓመት መጀመርያ ለኦሊምፒክ ብሄራዊ ቡድን መመረጡ ሲታወስ ለመጀመርያ ተሰላፊነትም ከሰዒድ ሐሰን ጋር ብርቱ ፉክክር ይጠብቀዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡