ፋሲል ከነማ ሁለተኛ ተጫዋች ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል

በካፍ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ የሚሳተፈው ፋሲል ከነማ ኪሩቤል ኃይሉን ለማስፈረም ስምምነት ላይ ደርሷል።

በተከላካይ አማካይ ስፍራ የሚጫወተው ይህ ተጫዋች የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ምሩቅ ሲሆን ያለፉትን ሁለት ዓመታት በደሴ ከተማ እግርኳስ ክለብ ያሳለፈ ሲሆን በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት አጋማሽ ወደ ደደቢት ቢያመራም ከመልቀቂያ ጋር በተያያዘ መፈረም ሳይችል ቀርቶ እንደነበር የሚታወስ ነበር።

በሁለት ዓመት ውል ክለቡን ይቀላቀላል ተብሎ የሚጠበቀው ኪሩቤል ስሙ ፌዴሬሽን እንደገባ ክለቡ የገለፀ ሲሆን ከእንየው ካሳሁን በመቀጠል ባህር ዳር ላይ በሚደረገው የቅድመ ውድድር ዝግጅት ቡድኑን የሚቀላቀል ሁለተኛ ተጫዋች ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡