ቶኪዮ 2020| ለሉሲዎቹ ዝግጅት 23 ተጫዋቾች ተጠርተዋል

በ2020 የቶኪዮ ኦሊምፒክ የሴቶች እግርኳስ የአፍሪካ ዞን ማጣርያ ካሜሩንን የሚገጥሙት የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሰላም ዘርዓይ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል።

ዩጋንዳን አሸንፈው ወደ ቀጣይ ዙር ያለፉት ሉሲዎቹ ሉሲዎቹ ነሐሴ 20 ከካሜሩን ጋር ባህር ዳር ላይ ለሚያደርጉት ጨዋታ ከነሐሴ 1 ጀምሮ ዝግጅታቸውን ማከናወን የሚጀምሩ ሲሆን ነሐሴ 11 ከኬንያ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ያደርጋሉ ተብሏል።

የተጫዋቾች ዝርዝር

ግብ ጠባቂዎች፡ ማርታ በቀለ (መከላከያ)፣ ታሪኳ በርገና (ጥረት ኮርፖሬት)፣ ዓባይነሽ ኤርቄሎ (ሀዋሳ ከተማ)

ተከላካዮች፡ መስከረም ካንኮ (አዳማ ከተማ)፣ ገነሜ ወርቁ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ መሠሉ አበራ (መከላከያ)፣ ቅድስት ዘለቀ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ብዙዓየሁ ታደሰ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ናርዶስ ጌትነት (አዳማ ከተማ)፣ ዓለምነሽ ገረመው (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)፣ ነጻነት ጸጋዬ (አዳማ ከነማ)፣ እፀገነት ብዙነህ (አዳማ ከተማ)

አማካዮች፡ ሕይወት ደንጌሶ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ እመቤት አዲሱ (መከላከያ)፣ ብርቱካን ገ/ክርስቶስ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ሰናይት ቦጋለ (አዳማ ከተማ)፣ አረጋሽ ከልሳ (መከላከያ)

አጥቂዎች፡ ምርቃት ፈለቀ (ሐዋሳ ከተማ)፣ ሎዛ አበራ (አዳማ ከተማ)፣ መዲና ጀማል( ሀዋሳ ከተማ)፣ ሴናፍ ዋቁማ (አዳማ ከተማ)፣ ሰርካዲስ ጉታ (አዳማ ከነማ)፣ ሔለን እሸቱ(መከላከያ)


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡