ፋሲል ከነማ የአሰልጣኝ ቅጥር ማስታወቂያ አውጥቷል


የኢትዮጵያ ዋንጫን ያሸነፈው ፋሲል ከነማ አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር የቅጥር ማስታወቂያ ይፋ አድርጓል።

የውድድር ዓመቱን በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ስር ያሳለፈው ክለቡ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ ከታንዛኒያው አዛም ጋር ከተጫወተ በኋላ ከአሰልጣኙ ጋር በይፋ የሚለያይ ሲሆን በምትኩ አሰልጣኝ ለመቅጠርም ለመጪዎቹ ሦስት ቀናት የሚቆይ ማስታወቂያ አውጥቷል።

ማስታወቂያው ይህንን ይመስላል፡-