ሴካፋ ከ15 በታች | ዩጋንዳ እና ሩዋንዳ ተጋጣሚዎቻቸውን በሰፊ ልዩነት አሸንፈዋል

በትናንትናው ዕለት የተጀመረው የሴካፋ ከ15 ዓመት በታች ዋንጫ ዛሬም ሲቀጥል ዩጋንዳ እና ሩዋንዳ ተጋጣሚዎቻቸውን በተመሳሳይ ውጤት 3-0 አሸንፈዋል።

መጀመርያ ጨዋታቸውን ያካሄዱት ዩጋንዳ እና ኢትዮጵያ ሲሆኑ ዩጋንዳ ከዕረፍት በፊት አንድ ከዕረፍት በኃላ ደሞ ሁለት ጎሎች በመጨመር ኢትዮጵያን በማሸነፍ ምድቡን ከሩዋንዳ ጋር በእኩል ነጥብ እና ግብ ክፍያ መምራት ጀምራለች።

ከጨዋታው በኃላም ኢትዮጵያ ሰባት የሚደርሱ የዩጋንዳ ተጫዋቾች ላይ የዕድሜ ተገቢነት ክስ ማስገባትዋ ፌዴሬሽኑ በይፋዊ ድረ ገፁ ገልጿል።

ቀጥሎ የተካሄደው የሩዋንዳ እና የደቡብ ሱዳን ጨዋታ ሲሆን በጨዋታውም ሩዋንዳ 3-0 ማሸነፍ ችላለች። በጨዋታው ኤሪክ ኢራሃምየ የተባለ የሩዋንዳ ተጫዋች ከዕረፍት በኃላ ሶስት ግቦች በማስቆጠር ሃትሪክ ሰርቷ። የውድድሩ ኮከብ ጎል አግቢነትም በሦስት ጎሎች እየመራ ይገኛል።

ውድድሩ ነገም ሲቀጥል በ08;00 ኬንያ ከ ሱዳን ፣ በ10;30 ደግሞ ብሩንዲ ከ ሶማልያ ያገናኛል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡