ወልቂጤ ከተማ ግብ ጠባቂ አስፈረመ

በርካታ ተጫዋቾችን በማስፈረም የሚመራው ወልቂጤ ከተማ ግብ ጠባቂው ይድነቃቸው ኪዳኔን ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል።

በኢትዮጵያ ቡና የእግርኳስ ህይወቱን ጅማሮ አድርጎ ወደ መከላከያ ካመራ በኋላ ከ10 ዓመታት በላይ በጦሩ ቤት ቆይታ ያደረገው ይድነቃቸው ወደ አዲስ አዳጊው ወልቂጤ ማምራቱን ተከትሎ በክለቡ ለተሰላፊነት ከካሜሩናዊው ቤሊንጌ ኢኖህ ጋር ይፎካከራል።

ወልቂጤ ከተማ እስካሁን ይድነቃቸውን ጨምሮ 11 ተጫዋቾች አስፈርሟል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡