ወላይታ ድቻ የ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ለሆነው ቡድኑ ሽልማት አበረከተ

ወላይታ ድቻ በአዳማ ሲደረግ በነበረው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ የማጠቃለያ ውድድር ላይ ተሳታፊ በመሆን አሸናፊ ለሆነው ቡድኑ ሽልማት አበርክቷል።

ከመከላከያ ጋር በነጥብ ዕኩል ሆኖ በግብ ልዩነት በመብለጥ የ2011 አሸናፊ መሆኑን ከትላንት በስቲያ ያረጋገጠው ክለቡ ሶዶ ሲደርስ አቀባበል የተደረገለት ሲሆን የ3 መቶ ሺህ ብር የማበረታቻ የገንዘብ ድጋፍን 30 ለሚደርሱ የልዑካን አባላት አበርክቷል። አቶ አሰፋ ሆሲሶ ለሶከር ኢትዮጵያ እንደገለፁት የወላይታ ዞን የመቶ ሺህ ብር እንዲሁም ደግሞ ክለቡ ሁለት መቶ ሺህ ብር በጋራ አበርክተዋል።

በአዳማ ውድድሩ ሲደረግ የዋናው ቡድን አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ በስፍራው የነበሩ ሲሆን ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴን ማድረግ የቻሉ በርከት ያሉ ተጫዋቾችንም እንደሚያሳድጉ ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡