ቻምፒዮንስ ሊግ | የመቐለ እና ካኖ ስፖርትን ጨዋታ ጅቡቲያዊያን ዳኞች ይመሩታል

መቐለ 70 እንደርታ ከካኖ ስፖርት አካዳሚ በመጪው እሁድ የሚያካሂዱትን ጨዋታ የሚመሩት ዳኞች ታውቀዋል።

ዋና ዳኛው ሳዳም መንሱር ሑሴን ፣ የመስመር ረዳች ዳኞች ሳልሕ ዓብዲ መሐመድ እና ሊበን መሐመድ ዓብዱልረዛቅ ሲሆኑ አራተኛው ዳኛ ደግሞ ቢላል ኢስማኤል ዓብደላ ናቸው። ለጨዋታው የተመደበው ኮምሽነር ደግሞ ሱዳናዊው ዓሚር ዑስማን መሐመድ ናቸው።

በተያያዘ ዜና የጨዋታው መግቢያ ዋጋ በይፋዊ የፌስ ቡክ ገፃቸው ይፋ ያደረጉት ምዓም አናብስት ክብር ትሪቡን ሦስት መቶ ብር ፣ መደበኛ አንድ መቶ ብር ፣ አንደኛ ፎቅ ደግሞ ሃምሣ ብር መሆኑ ሲገልፁ በዋጋው ላይ ለተነሱት ጥያቄዎች አስመልክተው ሰፋ ያለ መግለጫ በገፃቸው ሰጥተዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡