ቻምፒየንስ ሊግ| ካኖ ስፖርት አካዳሚዎች አዲስ አበባ ገብተዋል

በቻምፒየንስ ሊጉ ቅድመ ማጣርያ የመልስ ጨዋታ የመቐለ 70 እንደርታ ተጋጣሚ የሆኑት ካኖ ስፖርት አካዳሚዎች ትናንት አመሻሽ አዲስ አበባ ገብተዋል።

በውድድሩ እንደ መቐለ ሁሉ የመጀመርያ ተሳትፏቸውን እያደረጉ የሚገኙት ካኖዎች በትናንትናው ዕለት አዲስ አበባ በመግባት አፎሊ ሆቴል ማረፍያቸውን ሲያደርጉ ለኢኳቶርያል ጊኒ ብሄራዊ ቡድን ያስመረጧቸው የቡድኑ ወሳኝ ተከላካይ ቪሴንቴ አሲሙ እና አጥቂው ልዊስ ሚግዌል ኔቮን ጨምሮ የመጀመርያው ዙር ጨዋታ ያካሄደው ሙሉ የቡድን አባላት ይዘው ነው ኢትዮጵያ የገቡት።

ክለቡ ዛሬ አስር ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ልምምድ እንደሚያደርግ ለማወቅ የተቻለ ሲሆን ቅዳሜ ጠዋት ጨዋታ ወደሚያካሂድበት መቐለ በማምራት የመጨረሻ ልምምዱን አከናውኖ እሁድ የመልሱን ጨዋታ የሚያከናውን ይሆናል።

ማላቦ በተካሄደው የመጀመርያው ዙር የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ካኖ ስፖርት አካዳሚዎች መቐለን በጠባብ ውጤት 2-1 አሸንፈዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡