ዮሃንስ ሳህሌ የተጫዋች እና የአሰላለፍ ለውጥ አድርገው አንጎላን ይገጥማሉ 

 

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የምድቡን የመጨረሻ ጨዋታ ዛሬ በ11፡00 አንጎላን በአማሆሮ ስታድየም ይገጥማል፡፡ አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌም አንጎላን የሚገጥመው ቡድናቸውን መርጠዋል፡፡

በጉዳት ከዛሬው ጨዋታ ውጪ በሆነው አቤል ማሞ ምትክ በቋሚ አሰላለፉ ውስጥ የተካተተው ይድነቃቸው ኪዳኔ ለመጀመርያ ጊዜ በቻን የመሰለፍ እድል ሲያገኝ አማካዩ ተስፋዬ አለባቸው ሌላው በጉዳት ላይ የሚገኘው ጋቶች ፓኖምን ተክቶ በመጀመርያ አሰላለፍ ውስጥ ተካቷል፡፡ በሰፊ ግብ የማሸነፍ ግዴታ ውስጥ የገቡት አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ታፈሰ ተስፋዬን ከ ሙሉአለም ጥላሁን ጋር ማጣመርን የማጥቃት ምርጫቸው አድርገዋል፡፡ የአጥቂ አማካዩ ኤልያስ ማሞም ከመጀመርያ አሰላለፉ ውጪ ሆኗል፡፡

የዛሬው አሰላለፍ ይህንን ይመስላል

ይድነቃቸው ኪዳኔ

ስዩም ተስፋዬ – ያሬድ ባየህ – አስቻለው ታመነ – ተካልኝ ደጀኔ

በኃይሉ አሰፋ – ተስፋዬ አለባቸው – አስራት መገርሳ – ራምኬል ሎክ

ታፈሰ ተስፋዬ – ሙሉአለም ጥላሁን

PicsArt_1453718737638

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *