ዋልያዎቹ የምድብ 2 ግርጌን ይዘው ከቻን ተሰናበቱ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የመጨረሻ የምድብ ጨዋታውን ዛሬ 11፡00 ላይ በኪጋሊ አማሆሮ ስታየም ከአንጎላ ብሄራዊ ቡድን ጋር አድርጎ 2-1 ተሸንፏል፡፡ በካሜሩን እና ኮንጎ ጨዋታ ውጤት ላይ ተንተርሶ ጠባብ የማለፍ ተስፋ ይዞ ወደ ሜዳ የገባው ብሄራዊ ቡድናችን የመጀመርያ የቻን ውድድር ጎሉንም አግኝቷል፡፡

አስቀድማ ከምድቧ መውደቋን ያረጋገጠችው አንጎላ አሪይ ፓፔል በ54 እና 73ኛው ደቂቃ ባስቆጠራቸው ግቦች 2-0 መምራ ስትችል አምበሉ ስዩም ተስፋዬ በ75ኛው ደቂቃ ኢትዮጵያን ወደ ጨዋታው የመለሰች ግብ ማስቆጠር ቢችልም በቻን ታሪክ ኢትዮጵያ ያስቆጠረችው የመጀመርያ ግብ ሆኖ ከመመዝገብ የዘለለ አልሆነም፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ የመጨረሻውን ደረጃ ይዛ ስታጠናቅቅ ዲ.ሪ ኮንጎን 3-1 ያሸነፈችው ካሜሩን ምድቡን በበላይነት በማጠናቀቅ ወደ ሩብ ፍፃሜው ማለፏን ያረጋገጠች 5ኛዋ ሃገር ሆናለች፡፡ አስቀድማ ማለፏን ያረጋገጠችው ዲ.ሪ. ኮንጎ በ6 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ይዛ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅላለች፡፡

የምድብ ለ የደረጃ ሰንጠረዥ ይህንን ይመስላል፡-

12615531_1031688286891857_2330745984961866011_o

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *