አሥራት ቱንጆ ከቡና ጋር ይቀጥላል

ከሰበታ ከተማ ጋር በቃል ደረጃ ተስማምቶ የነበረው አሥራት ቱንጆ ወደ ኢትዮጵያ ቡና ተመልሶ ፊርማውን አኑሯል።

ባለፈው ሳምንት በቃል ደረጃ ለሰበታ ከተማ ለመፈረም ተስማምቶ የነበረው አሥራት በመጨረሻው ሰዓት ከአዲስ አዳጊው ክለብ የቀረበለት ውል ላይ ለውጥ በመደረጉ ምክንያት ሳይስማማ በመቅረቱ ባለፈው ውድድር ዓመት ወዳሳለፈበት ኢትዮጵያ ቡና ተመልሶ ፊርማውን አኑሯል።

በ2009 ክረምት ጅማ አባ ጅፋርን ለቆ ቡናን የተቀላቀለውና በተለይ ባለፈው ዓመት በግሉ ጥሩ ጊዜ ያሳለፈው ይህ አማካይ በዚህ ዝውውር መስኮት ለኢትዮጵያ ቡና የፈረመ ስድስተኛ ተጫዋች ሆኗል።


© ሶከር ኢትዮጵያ