ፍቅረየሱስ ተ/ብርሀን መከላከያን ተቀላቀለ

በዝውውሩ የነቃ ተሳትፎ እያደረገ የሚገኘው መከላከያ አሁን ደግሞ የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ፍቅረየሱስ ተ/ብርሀንን የግሉ ማድረግ ችሏል።

የቀድሞው የኤሌክትሪክ ተጫዋች ፍቅረየሱስ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ለቆ ወደ ወደ ሀዋሳ ከተማ ካመራ በኋላ ሁለት የውድድር ዓመታትን በመልካም እንቅስቃሴ ያሳለፈ ሲሆን ወደ ሲዳማ ቡና ለማምራት ከስምምነት ቢደርስም ዝውውሩን ሳያጠናቅቅ ወደ ጦሩ ቤት አምርቷል። ከመከላከያ ጋርም ለሁለት ዓመታት የሚያቆየውን ፊርማ ማኖር ችሏል።

የፍቅረየሱስ መፈረም የአማካይ ክፍል ተጫዋቾችን ለለቀቀው መከላከያ አማራጮች ያሰፋለታል ተብሎ ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ