ውበቱ አባተ ነገ በይፋ የሰበታ ከተማ አሰልጣኝ ይሆናሉ

ሰበታ ከተማ ነገ በጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ ውበቱ አባተን አዲሱ አሰልጣኝ አድርጎ በይፋ ይሾማል።

የውድድር ዓመቱን በፋሲል ከነማ ያሳለፉትና ከቡድኑ ጋርም የኢትዮጵያ ዋንጫን ያነሱት አሰልጣኝ ውበቱ ከፋሲል ጋር ከተለያዩ በኋላ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ሳየስማቸው ሲያያዝ ቢቆይም ወደ ሰበታ ለማምራት መስማማታቸው የሚታወስ ነው። በዚህም መሠረት ነገ ነሐሴ 25 በሚሰጥ ጋዜጣዊ መግለጫ በይፋ የሰበታ ከተማ አሰልጣኝ ሆነው ይሾማሉ።

ዓለምገና በሚገኘው ዓለም ሆቴል ከጠዋቱ 3:00 የቡድኑ አመራሮች በተገኙበት በሚሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ከሰበታ ከተማ ጋር ስለሚኖራቸው ቆይታ እና ስምምነት ዝርዝር እንዲሁም ቀጣይ እቅድ ዙርያ ማብራርያ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ