ብስራት ገበየሁ ኢትዮጵያ ቡናን ተቀላቀለ

ኢትዮጵያ ቡና የወልቂጤ አምበል የነበረው ብስራት ገበየሁን የክለቡ ሰባተኛ ፈራሚ አድርጎ ወደ ቡድኑ መቀላቀሉን አስታውቋል።

ከቅዱስ ጊዮርጊስ ወጣት ቡድን አድጎ በወልቂጤ ከተማ ያለፉት 7 ዓመታትን ያሳለፈው ብስራት በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ክለቡ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እንዲያድግ ወሳኝ ሚና የተጫወተው እና ቡድኑንም በአምበልነት ሲመራ የነበረው ብስራት ከዓለም አንተ ካሳ በመቀጠል ለቡድኑ የፈረመ ሁለተኛው የአማካይ ሥፍራ ተጫዋች ሆኗል።

በዚህ ሳምንት ተጫዋቾች ማስፈረም የጀመረው ኢትዮጵያ ቡና እስካሁን ብስራት እና በወልቂጤ የቡድን ጓደኛው የነበረው ሐብታሙ ታደሰን ጨምሮ ሰባት ተጫዋቾችን አስፈርሟል።


© ሶከር ኢትዮጵያ