ወልዋሎ ግብ ጠባቂ አስፈረመ

እስካሁን አስራ ሦስት ተጫዋቾች ያስፈረሙት ቢጫ ለባሾቹ በግብ ጠባቂ ላይ ያላቸውን ክፍተት ለመድፈን ወደ ጃፋር ደሊልን አስፈርመዋል።

ከአዳማ ወጣት ቡድን አድጎ ክለዩ በ2006 ወደ ፕሪምየር ሊጉ ሲመለስ ትልቅ ድርሻ የነበረው ግብ ጠባቂው ባለፈው የውድድር ዓመት አጋማሽ ቡድኑ ሁለት የውጭ ዜግነት ያላቸው ግብ ጠባቂዎች በማስፈረሙ ከቡድኑ ጋር መለያየቱ ይታወሳል። መለሎው ግብ ጠባቂ ባለፉት ዓመታት ከወልዋሎ ጋር ጥሩ ቆይታ የነበረው እና በቀጣይ ቀናት ወደ ሌላ የፕሪምየር ሊግ ክለብ ያመራል ተብሎ የሚጠበቀው በረከት አማረን ቦታ ይተካልም ተብሏል።

በተያያዘ ዜና ወልዋሎዎች ባለፈው የውድድር ዓመት ከጅማ አባ ቡና ጋር ላሳለፈው ካርሎስ ዳምጠው እና ሶሎዳ ዓድዋ ወደ ከፍተኛ ሊግ እንዲያድግ ከፍተኛ ድርሻ ለነበራቸው ጠዓመ ወ/ኪሮስ እና ክብሮም ዘርዑ የሙከራ ዕድል መስጠታቸውን ለማወቅ ተችሏል።


© ሶከር ኢትዮጵያ