የወልዋሎ ተጫዋቾች ክለቡ ላይ ቅሬታቸውን አሰምተዋል

የወልዋሎ ተጫዋቾች የሰኔ ወር ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው ገልፀው ለፌዴሬሽኑ አቤቱታ አቅርበዋል፡፡

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በወልዋሎ ክለብ ውስጥ ሲጫወቱ የነበሩት 13 ተጫዋቾች በቅሬታቸው በክለቡ ውል እያለን የሰኔ ወርን ደሞዝ አልከፈለንም፤ እስከ አሁን በተደጋጋሚ ክለቡ ክፍያን እንዲፈፅም ብንጠይቅም ተግባራዊ ሊያደርግ አልቻለም። ስለዚህ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን በገባነው ውል መሠረት ተፈፃሚ ያድርግን ሲሉ ቅሬታቸውን በደብዳቤ ገልጸዋል፡፡

በጉዳዩ ዙርያ ከክለቡ ኃላፊዎች ባገኘነው ምላሽ በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ደሞዛቸው ሊዘገይ እንደቻለ እና በቅርብ ቀናት ክፍያቸው እንደሚፈፀም ተገልጿል።

ደብዳቤው ይህን ይመስላል


© ሶከር ኢትዮጵያ