ባህር ዳር ከተማ ተጨማሪ ተጫዋች አስፈርሟል

በዝውውሩ በንቃት እየተሳተፈ የሚገኘው ባህር ዳር ከተማ ሰለሞን ወዴሳን ስድስተኛ ፈራሚ አድርጓል፡፡
ከሀዋሳ ከተማ ወጣት ቡድን ከተገኘ በኃላ በወጣት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ ጊዜ ተጠርቶ መጫወት የቻለው እና በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በመድን የአማካይ ተከላካይ ሥፍራ ጥሩ ግልጋሎት ሲሰጥ የነበረው ሰለሞን ወዴሳ የጣና ሞገዶቹን በሁለት ዓመት ውል ተቀላቅሏል፡፡

ከተከላካይ አማካይነት በተጨማሪ በተከላካይ ስፍራ የሚጫወተው ይህ ተጫዋች ከሀያ ቀናት በፊት በወላይታ ድቻ ለመጫወት የተስማማ ቢሆንም ዝውውሩን ሳያጠናቅቅ በመቅረት ወደ ባህር ዳር አምርቷል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ