የሴካፋ ከ15 ዓመት በታች ውድድር በዩጋንዳ አሸናፊነት ተጠናቀቀ

ላለፉት ሳምንታት በኤርትራ አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው የሴካፋ ከ15 ዓመት በታች ውድድር ዛሬ ሲጠናቀቅ ዩጋንዳ የዋንጫ አሸናፊ ሆናለች። ሩዋንዳ ደግሞ ሦስተኛ ደረጃ ይዛለች።

ቀድሞ 7:30 የተካሄደው የብሩንዲ እና ሩዋንዳ የደረጃ ጨዋታ ሲሆን መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ አንድ ለአንድ ተጠናቆ ወደ መለያ ምት በማምራት ሩዋንዳ 4-2 በማሸነፍ ሦስተኛ ደረጃ ይዛ ማጠናቀቅ ችላለች።

ቀጥሎ የተካሄደውና 10:00 የተጀመረው የፍፃሜው ጨዋታ በዩጋንዳ እና ኬንያ መካከል ተከናውኖ ዩጋንዳ ከፍፁም ብልጫ ጋር 4-0 በማሸነፍ ለመጀመርያ ጊዜ የተዘጋጀው ዋንጫ ተሸላሚ ሆናለች። የዩጋንዳ ጎሎች የተቆጠሩት በኦግዋ ዴቪስ ፣ ትራቪስ ሙታይባ እና ኬዩኔ አባስ (2) ነው።

የኤርትራው ተመስገን ተስፋይ ግምት አግኝቶ ከነበረው የዩጋንዳው ትራቪስ ሙታይባ በመብለጥ የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች ሆኖ ተሸልሟል።


© ሶከር ኢትዮጵያ