ኢትዮጵያ ቡና ታፈሰ ሰለሞንን አስፈረመ

ኢትዮጵያ ቡናዎች ስሙ ከበርካታ ክለቦች ጋር ሲያያዝ የቆየው ታፈሰ ሰለሞንን ማስፈረም ችለዋል።

የቀድሞው የኒያላ፣ ኤሌክትሪክ እና አህሊ ሸንዲ የአጥቂ አማካይ ያለፉትን አምስት ዓመታት ካሳለፈበት ሀዋሳ ከተማ ጋር የነበረው ውል መጠናቀቅን ተከትሎ በበርካታ ክለቦች ሲፈለግ እንደመቆየቱ ማረፊያው አነጋጋሪ የነበረ ሲሆን በመጨረሻም ምርጫውን ኢትዮጵያ ቡና አድርጓል።

ባለፈው የውድድር ዓመት የአጥቂ አማካይ ተጫዋቾች እና የጎል ዕድል በመፍጠር ረገድ ጉልህ ክፍተት የነበረባቸው ኢትዮጵያ ቡናዎች ለ2 ዓመታት ባስፈረሙት ታፈሰ ሰለሞን ችግራቸውን ይቃልላሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ኢትዮጵያ ቡና ከዚህ ቀደም ስድስት ተጫዋቾችን ያስፈረመ ሲሆን ታፈሰ የቡድኑ ሰባተኛ አዲስ ተጫዋች ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ