ኢትዮጵያ ቡና አዲስ ግብጠባቂ ለማስፈረም ተስማማ

በረከት አማረ ኢትዮጵያ ቡናን ለመቀላቀል ሲስማማ በቅርብ ቀናት በይፋ ይፈራረማል።

ላለፉት ሦስት ዓመታት በወልዋሎ ቆይታ ያደረገው እና በተለይም በ2009 ቡድኑ ወደ ፕሪምየር ሊግ ሲያድግ ምርጥ ብቃት በማሳየት የውድድሩ ኮከብ ግብ ጠባቂ ተብሎ የተሸለመው በረከት ከጥቂት ሰዓታት በፊት የህክምና ምርመራውን በተሳካ ሁኔታ ያለፈ ሲሆን በቀጣይ ቀናት በይፋ ለክለቡ ፊርማውን አኑሮ ይቀላቀላል ተብሎ ይጠበቃል።

ላለፉት ዓመታት በግሉ ከወልዋሎ ጋር የስኬት ዓመታት ያሳለፈው የቀድሞው የአውስኮድ ግብጠባቂ ባለፈው ዓመት በጊኒያዊው ዓብዱልዓዚዝ ኬታ የቋሚነት ቦታ የተነጠቀ ሲሆን ከዚህ ቀደም በሴካፋ ዋንጫ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ወክሎ ተጫውቷል። በኢትዮጵያ ቡናም ለቀዳሚ ተመራጭነት ከሌላው አዲስ ፈራሚ ተክለማርያም ሻንቆ ጋር ይፎካከራል።


© ሶከር ኢትዮጵያ