የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለሴካፋ ውድድር ዝግጅት ጀመረ

በዩጋንዳ አዘጋጅነት መስከረም ወር ላይ ለሚካሄደው የሴካፋ ከ20 ዓመት ውድድር የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ በማድረግ ዝግጅቱን ጀመረ።

በአሰልጣኝ ዮሴፍ ተስፋዬ በሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ከተደረገላቸው 23 ተጨዋቾች መካከል የሀዋሳ ከተማው መስፍን ታፈሰ ከዋናው ብሔራዊ ቡድን ጋር በባህር ዳር ዝግጅት ላይ የሚገኝ በመሆኑ ሳይገኝ ሲቀር የተቀሩት 22 ተጫዋቾች በተገኙበት የተሟላ ዝግጅቱን ለማድረግ ወደ አዳማ ከተማ አቅንቷል።

የተመረጡት ተጫዋቾች የሚከተሉት ናቸው፡-

ግብ ጠባቂዎች፡ ተመስገን ዮሐንስ (ቅ/ጊዮርጊስ)፣ ዳዊት ባህሩ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ምንተስኖት ጊምቦ (ሀዋሳ ከተማ)

ተከላካዮች፡ ፉአድ ነስሩ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ያብስራ ሙሉጌታ (ቅ/ጊዮርጊስ)፣ ፀጋአብ ዮሐንስ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ኢያሱ ለገሠ (አዲስ አበባ ከተማ )፣ አቡበከር ሙራድ (ቅ/ጊዮርጊስ)፣ ቃልአብ ፍቅሩ (ኢትዮጵያ ቡና )፣ መስፍን ጳውሎስ (መከላከያ)፣ እዮብ ማቲያስ (አዳማ ከተማ)

አማካዮች፡ ሙሴ አበለ (ኢትዮጵያ ቡና )፣ ብሩክ መንገሻ (አዳማ ከተማ)፣ አድናን ረሻድ (አምቦጎል ኘሮጀክት)፣ ወንድማገኝ ኃይሉ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ዊሊያም ሰለሞን (መከላከያ)፣ አበባየሁ ሀጂሽ (ወላይታ ድቻ)

አጥቂዎች፡ መስፍን ታፈሰ (ሀዋሳ ከተማ)፣ እዮብ ዓለማየሁ (ወላይታ ድቻ)፣ አቤል ነጋሽ (መከላከያ)፣ ታምራት ስላስ (ወላይታ ድቻ)


© ሶከር ኢትዮጵያ