ኢትዮጵያዊያን ዳኞች የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታን ይመራሉ

የ2022 ዓለም ዋንጫ የአፍሪካ ሀገራት ቅድመ ማጣርያ ጨዋታዎች ከቀናት በኋላ መካሄድ ሲጀምሩ ኢትዮጵያውያን ዳኞችም ወደ ሲሸልስ ያመራሉ።

በመጪው ሀሙስ 9:00 ቪክቶርያ ላይ ሲሺልስ ከ ሩዋንዳ የሚደርጉትን የመጀመርያ ጨዋታ በላይ ታደሰ ዋና ዳኛ፣ ክንዴ ሙሴ እና ትግል ግዛው ረዳት ዳኞች እንዲሁም አራተኛ ዳኛ ቴዎድሮስ ምትኩ እንዲሆኑ ተመድበዋል።

በላይ ታደሰ እና ረዳቶቹ (ከትግል ግዛው በቀር) ባሳለፍነው ሳምንት በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የሱዳኑ ኤል ሜሪክ ከአልጀሪያው ጂኤስ ካባሊ ያደረጉትን የመልስ ጨዋታ መምራታቸው የሚታወስ ነው።


© ሶከር ኢትዮጵያ