የመቐለ ባሎኒ ፉትሳል ውድድር ተጠናቀቀ

ላለፉት ሦስት ሳምንታት በባሎኒ ትንሿ ስታዲየም ሲካሄድ የቆየው ውድድር ዛሬ ተጠናቀቀ። የደደቢቶቹ ሙሉጌታ ዓምዶም እና ቢንያም ደበሳይ፣ የስሑል ሽረው አርዓዶም ገብረህይወት እና ሌሎች የያዘው ራሄል ቡናም ውድድሩን አሸንፏል።

ደማቅ ድጋፍ እና ጠንካራ ፉክክር የታየበት ጨዋታው በመደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ አራት ለአራት ሲጠናቀቅ አሸናፊው ለመለየት በተሰጠ ፍፁም ቅጣት ምት አንጋፋ ተጫዋቾች የያዘው ራሄል ቡና ማይሊሓምን በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል።

የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች ኄኖክ ገ\እግዚአብሔር፣ ኮከብ አሰልጣኝ ሃፍቶም ማሞ እንዲሁም የዋንጫ ተፋላሚው ማይሊሐም ግብ አስቆጣሪ ዐቢይ ተወልደ በ37 ግቦች ኮከብ ግብ አስቆጣሪ ሆኖ ተሸልሟል።

በአቶ ሃፍቱ ገ/የሱስ አዘጋጅነት ከወትሮው በተለየ የደጋፊዎች ድምቀት የተካሄደው ይህ ዓመታዊ ውድድር በቀጣይ ዓመትም በተሻለ ቅድመ ዝግጅት እንደሚቀጥል ተገልጿል።


© ሶከር ኢትዮጵያ