ኳታር 2022 | አዞዎቹ ዛሬ ኢትዮጵያ ይገባሉ

በዓለም ዋንጫ ማጣርያ ኢትዮጵያን የሚገጥመው የሌሶቶ ስብስብ ሲታወቅ በዛሬው ዕለት ኢትዮጵያ እንደሚገባ ይጠበቃል።

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ደቡብ አፍሪካዊው ቴቦ ሴኖንግን ዋና አሰልጣኝ አድርገው የቀጠሩት ሌሶቶዎች በቀጣይ ሳምንት ኢትዮጵያን የሚገጥመው ስብስባቸውን ይፋ ሲያደርጉ በዛሬው ዕለት ወደ አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ባለፈው ወር በቀድሞው ዋና አሰልጣኝ ህመም ምክንያት በቴክኒካል ዳይሬክተሩ ሌስሊ ኖትሲ የተጫዋቾች ምርጫ ያደረጉት ሌሶቶዎች በአዲሱ አሰልጣኛቸው ብዙ ተስፋ አድርገው ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ።

ኢትዮጵያን የሚገጥመው የአዞዎቹ ስብስብ የሚከተለውን  ይመስላል

ግብ ጠባቂዎች፡ ታቢሶ ሊቻባ፣ ሊካኖ ሙፑቲንግ 

ተከላካዮች፡ ባስያ ማኬባ፣ ሞትሎሜሎ ምክዋናዚ፣ ንካው ሌሮቶሊ፣ ጆን ሞሃይ፣ ሮታቢ ሞኮኮና፣ ሮታቢ ራሴቱሳ፣ ኦናኤሌ ኮቴሎ

አማካዮች፡ ሴቦ ቶላኔ፣ ሊሴማ ሎቦኮሎኔ፣ ጃኔ ታቤንሶ፣ ሂሎምፎ ካላኬ፣ ሊህሎሆሎ ፎታኔ፣ ኒዮ ሞካቻኔ፣ ሶሬሎ ብሬንግ፣ ቱሜሎ ኩትህላንግ፣ ማካራ ታይሳኔ

አጥቂዎች፡ ሞኮኔ ማራቤ፣ ሞትባንግ ሴራ፣ ኮቶ ማሳቢ፣ ሴፎ ሴትሩማኔ