መከላከያ የግራ መስመር ተከላካይ አስፈረመ

በዝውውር መስኮቱ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ የሚገኘው እና በቅርቡ ወደ ዝግጅት የሚገባው መከላከያ የግራ መስመር ተከላካይ አስፈርሟል።

ከሀዋሳ ከነማ የታዳጊ ቡድን አንስቶ እስከ ዋናው ቡድን ድረስ አምበል በመሆን ጭምር መጫወት የቻለው ደስታ ዮሐንስ ያለፉትን አራት ዓመታት በግራ መስመር ተከላካይነት ጥሩ ብቃት በማሳየት ጎልተው ከወጡ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነበር። ደስታ ከሀዋሳ ከተማ ውጪ በየትኛውም የፕሪምየር ሊግ ቡድን ያልተጫወተ ሲሆን ቀጣይ ክለቡን መከላከያ በማድረግ ለሁለት ዓመት የሚያቆየውን ፊርማውን አኑሯል።

ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መጫወት የቻለው ደስታ ባሳለፍነው ሁለት ዓመት በግራ የተከላካይ መስመር በኩል በሁነኛ ተጫዋች በማጣት ሲቸገሩ ለነበሩት መከላከያዎች ከአስናቀ ሞገስ ጋር በመሆን በቦታው ላይ የነበረውን ክፍተት ይቀርፋሉ ተብሎ ይገመታል።

መከላከያዎች በዝውውሩ ሂደት እስካሁን ምንተስኖት አሎ፣ አስናቀ ሞገስ፣ ሐብታሙ ወልዴ፣ አንተነህ ተስፋዬ፣ ነስረዲን ኃይሉ፣ ፍቅረየሱስ ተ/ብርሃን፣ ሐብታሙ ገዛኸኝ እና ደስታ ዮሐንስን ማስፈረም ችለዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ