ኢትዮጵያ ቡናዎች የሁለት ተጫዋቾች ዝውውር አጠናቀቁ

ባለፉት ሰባት ቀናት በዝውውሩ ንቁ ተሳትፎ ያደረጉት ኢትዮጵያ ቡናዎች በረከት አማረ እና አቤል ከበደን አስፈርመዋል።

ከጥቂት ቀናት በፊት በረከት አማረ ኢትዮጵያ ቡናን ለመቀላቀል መስማማቱ እና የህክምና ምርመራውን ማለፉን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ክለቡ ግብ ጠባቂውን ማስፈረሙን በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ አስታውቋል። በረከት በአውስኮድ እና ያለፉትን ዓመታት ደግሞ በወልዋሎ ያሳለፈ ሲሆን ለቋሚ ግብ ጠባቂነት ከሌላው አዲስ ፈራሚ ተክለማርያም ሻንቆ ጋር ይፎካከራል።

ሁለተኛ ክለቡን የተቀላቀለው ያለፈው የውድድር ዓመት ከወልዲያ ጋር ቆይታ ያደረገው የአጥቂ ክፍል ተጫዋቹ አቤል ከበደ ሲሆን ለቋሚ ተሰላፊነትም ከበርካታ ተጫዋቾች ፉክክር ይጠብቀዋል። ከመከላከያ ታዳጊ ቡድን የተገኘው የቀኝ መስመር አጥቂው በ2008 ወደ መከላከያ ዋናው ቡድን አድጎ ላለፉት ዓመታት በዋናው ቡድን ቆይታ ያደረገ ሲሆን ያለፉት አራት ወራትም ከወልዲያ ጋር ቆይታ አድርጓል።


© ሶከር ኢትዮጵያ