ኢትዮጵያ ቡና ጋዜጣዊ መግለጫ ጠርቷል

ኢትዮጵያ ቡና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ጋዜጣዊ መግለጫ የፊታችን ሐሙስ በኢንተርኮንትኔታል ሆቴል ጠርቷል።

ኢትዮጵያ ቡና ከ2008 ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ ፊቱን ከውጭ ሀገር አሰልጣኞች ወደሀገር ውስጥ አሰልጣኝ በማዞር ማሰቡን ተከትሎ የቀድሞ አሰልጣኙን ካሳዬ አራጌ ጋር ቅድመ ስምምነት በማድረጉ አሰልጣኙ ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱ ይታወቃል። አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌም በይፋ የኢትዮጵያ ቡና ዋና አሰልጣኝ መሆኑ የሚበሰርበት እና የወደፊት እቅዱን አስመልክቶ ማብራሪያ የሚሰጥበት ጋዜጣዊ መግለጫ የፊታችን ሐሙስ ነሐሴ 30 ቀን 2011 በኢንተርኮንትኔታል አዲስ ሆቴል 09:00 ይደረጋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ