ቶኪዮ 2020| የሉሲዎቹ የዛሬው ጨዋታ አሰላለፍ ታውቋል

በ2020 የቶኪዮ ኦሊምፒክ ሁለተኛ ዙር ማጣርያ ኢትዮጵያ ከካሜሩን የሚያደርጉት የመልስ ጨዋታ ዛሬ አመሻሽ ያውንዴ ላይ ይደረጋል።

በመጀመርያው ጨዋታ ባህር ዳር ላይ 1-1 መጠናቀቁ የሚታወስ ሲሆን በጨዋታው ተሰላፊ ከነበሩት መካከል በዛሬው ጨዋታ ናርዶስ ጌትነት እና ሰርካዲስ ጉታ ተጠባባቂ ሆነው ጎሉን ያስቆጠረችው ሰናይት ቦጋለ እና ህይወት ደንጊሶ በመጀመርያው አሰላለፍ ተካተዋል።

አሰልጣኝ ሰላም ከተጫዋቾች ለውጥ በተጨማሪ የሚና ለውጥ ያደረገች ሲሆን በአማካይ ስፍራ የመጀመርያውን ጨዋታ የጀመረችው ዓለምነሽ ገረመው ወደ መስመር ተከላካይነት ተሸጋሽጋለች። መሰለፏ አጠራጥሮ የነበረችው ብርቱካን ገብረክርስቶስም ይበልጥ የማጥቃት ሚና ተሰጥቷት ወደ ሜዳ እንደምትገባ ይጠበቃል።

የዛሬ የሉሲዎቹ አሰላለፍ ይህን ይመስላል፡-

ዓባይነሽ ኤርቀሎ

ዓለምነሽ ገረመው – መሠሉ አበራ – መስከረም ካንኮ – ብዙዓየሁ ታደሰ

ህይወት ደንጊሶ – ሰናይት ቦጋለ – እመቤት አዲሱ

ብርቱካን ገብረክርስቶስ – ሴናፍ ዋቁማ – መዲና ዐወል


© ሶከር ኢትዮጵያ