ቅዱስ ጊዮርጊስ ስርቢያዊ አሰልጣኝ ቀጠረ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በአሁኑ ሰዓት እያካሄደ ባለው ጋዜጣዊ መግለጫ አዲሱ የክለቡ ዋና አሰልጣኝን አስተዋውቋል።

አዲሱ የክለቡ አሰልጣኝ ሆነው የተቀጠሩት ሰርዳን ዚቮጅሆቭ የ47 ዓመት ሰርቢያዊ ሲሆኑ ከዚህ ቀደም በዩጋንዳው ቪላ እና በታንዛኒያው ያንጋ አፍሪካ ሰርተዋል። በጥር ወር ደግሞ ወደ ዛምቢያ አምርተው ቢዩልድ ኮንን እስከ ውድድር ዘመኑ መጨረሻ ድረስ አሰልጥነዋል።

ሰርዳን ከውጤታማው ሰርዮቪች ሚሉቲን (ሚቾ) እና ዱሳን ኮንዲች በኋላ ቅዱስ ጊዮርጊስን ያሰለጠኑ ሦስተኛው ሰርቢያዊ ሲሆኑ በሊጉ ደግሞ 2010 ላይ በኢትዮጵያ ቡና ከሰሩት ኮስታዲን ፓፒች በኋላ ወደ ኢትዮጵያ የመጡ የምስራቅ አውሮፓዊቷ ዜጋ አሰልጣኝ ሆነዋል ።

-ተጨማሪ መረጃዎች እና የጋዜጣዊ መግለጫውን ዘገባ ከቆይታ በኋላ ይዘን እንመለሳለን።


© ሶከር ኢትዮጵያ