አሰልጣኝ ገ/መድህን ኃይሌ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ መግለጫ ሰጡ

የፕሪምየር ሊጉ የሁለት ጊዜ አሸናፊ አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ በወቅታዊ ጉዳዮች ዛሬ ጠዋት በደስታ ሆቴል መግለጫ ሰጥተዋል።

ክለቡ እንዲያሟላላቸው ስለጠየቋቸው ቅድመ ሁኔታዎች፣ በክለቡ ደጋፊ ማኅበር ያለው የአሰራር ክፍተት እና ስለቀጣይ እቅዶቻቸው ሰፋ ያለ መግለጫ የሰጡት አሰልጣኙ አሁንም በክለቡ በርካታ መስተካከል ያሉበት ጉዳዮች እንዳሉ ገልፀው ችግሮቹን ለመፍታት ከክለቡ ጋር እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

ስለ ወቅታዊ የአህጉሪቱ የዝውውር ጉዳይ እና ስለ ክለቡ ወሳኝ ተጫዋቾች ቆይታ ገለፃ ያደረጉት አሰልጣኙ ክለባቸው የወቅቱ የተጫዋቾች የዋጋ ንረት እንዳሰሰው ገልፀው ወሳኝ ተጫዋቾቹን ለማቆየት ግን እስከ መጨረሻው እንደሚሰራ ገልፀዋል።

አሰልጣኙ የሰጡት ሙሉ ጋዜጣዊ መግለጫ እና ከጋዜጠኞች ተጠይቀው የሰጧቸውን ምላሾች በዝርዝር ከቆይታ በኋላ የምንመለስበት ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ