ስሑል ሽረ አይቮሪኮስታዊውን ተጫዋች አስፈረመ

ወደ ዝውውሩ ዘግይተው በመግባት ተጫዋቾች በማስፈረም ላይ የሚገኙት ስሑል ሽረዎች ሁለገቡ ዲድዬ ለብሪን የግላቸው አድርገዋል።

ከዚ ቀደም በበርካታ ክለቦች ቆይታ የነበረው የ30 ዓመቱ ሁለገብ ተጫዋች ስሑል ሽረ አስራ አንደኛ ክለቡ ሲሆን ለሱዳኑ አልሜሪክ ፣ ብሎምፎንቴን ሴልቲክ፣ ኤስፔረንስ እና ሴፋክስየን መጫወቱ ይታወሳል። በ2010 ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ በኋላም በኢትዮ ኤሌክትሪክ እና በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ደግሞ በጅማ አባ ጅፋር ቆይታን አድርጓል።

ዲዲዬ በፊት አጥቂነት፣ በመስመር አጥቂነት እና በአማካይነት ግልጋሎት መስጠት የሚችል ሲሆን በኢትዮጵያ በነበረው የሁለት ዓመት ቆይታ በመስመር ተጫዋችነት አብዛኛውን ጨዋታ አድርጓል። ባለፈው ዓመት ሁነኛ የመስመር ተጫዋች ያልነበራቸው ስሑል ሽረዎችም ተጫዋቹን ማስፈረማቸው ጥሩ አማራጭ ይፈጥራላቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

የናይጀርያዊው ግብ ጠባቂ ሰንደይ ሮትሚን ውል ያላራዘሙት ስሑል ሽረዎች አዲስ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም እንቅስቃሴ ጀምረዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ