ኢትዮጵያ ቡና አጥቂ አሰፈረመ

በአሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ እየተመራ በዝውውር ሂደቱ በንቃት እየተሳተፈ የሚገኘው ኢትዮጵያ ቡና አጥቂው እንዳለ ደባልቄን አስፈርሟል፡፡

የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ እንዳለ በ2010 የውድድር ዘመን ደግሞ ከጅማ አባጅፋር ጋር የሊጉን ዋንጫ ያሸነፈ ሲሆን ከደደቢት ጋርም የሊጉን ዋንጫ በክለቡ ቆይታው አግኝቷል፡፡ የተጠናቀቀውን የውድድር ዓመት ከጅማ አባ ጅፋር ለቆ ወደ ባህር ዳር በማምራት በጣና ሞገዶቹ ቤት የቆየው እንዳለ ከዚህ ቀደም በአሰልጣኝ ድራገን ፖፓዲች የአሰልጣኝነት ዘመን ወደ ኢትዮጵያ ቡና ለማምራት ከጫፍ ደርሶ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን በመጨረሻም በሁለት ዓመት ውል ቡናማዎቹን መቀላቀል ችሏል።

እስከ አሁን በጥቅሉ 12 ተጫዋቾችን ያስፈረመው ኢትዮጵያ ቡና ከመስከረም 5 ጀምሮ ወደ ቅድመ ውድድር ዝግጅት የሚገባ ይሆናል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ