የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ደብዳቤ አስገባ

የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን የሊግ አደረጃጀት (ፎርማት) ለውጥን አስመልክቶ ለኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ደብዳቤ አስገብቷል።

በሊግ ፎርማጥ ዙርያ ለውጥ ጥናት በማስጠናት እና የአዲስ አበባ ክለቦች ተዟዙሮ መጫወትን በማስቀረት በራሳቸው የውስጥ ውድድር (በአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ስር ለመወዳደር) ባሳለፍነው ወር ክለቦች የጋራ ስምምነት ፊርማ ማድረጋቸው ይታወቃል። ይህን ተከትሎ የአአ እግርኳስ ፈዴሬሽን የደረሰበትን ሂደት እና ድምዳሜ በጠቅላላ ጉባዓ ዕለት ለመግለፅ አጀንዳ ይያዝልኝ ሲል ለኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ደብዳቤ አስገብቷል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባዔ ጥቅምት 1 ቀን በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ፌዴሬሽኑ አስቀድሞ መግለፁ ይታወቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ