ፌዴሬሽኑ ጋዜጣዊ መግለጫ አዘጋጅቷል

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሊሰጥ ነው።

በበርካታ አሉታዊ እና አውንታዊ ጉዳዮች ላይ ተወጥሮ የአመራርነት ዘመኑን አንድ ዓመት ያስቆጠው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የፊታችን ሰኞ መስከረም 5 ቀን 08:30 ላይ ወሎ ሠፈር አካባቢ (ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፅህፈት ቤት ቢሮ) በሚገኘውና ፌዴሬሽኑ አዲስ በገዛው ህንፃ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫውን ይሰጣል።

በርካታ ጥያቄዎች እንደሚስተናገዱበት እና መልሶች እንደሚሰጡበት በሚጠበቀው በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በዋናነት በአደረጃጀት ለውጥ እና ፌዴሬሽኑ በቅርቡ ይፋ ባደረገው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊዎች 24 የመሆናቸው ውሳኔ ዙርያ ሰፊ ማብራሪያ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ