ቻን 2020| አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ ለ24 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል

በዛሬው ዕለት ዝግጅታቸው የሚጀምሩት ዋልያዎቹ ፍፁም ዓለሙ እና ፍቃዱ ዓለሙን ጨምሮ ስምንት ተጫዋቾችን ቀላቅለው በአጠቃላይ በ24 ተጫዋቾች ዝግጅት ይጀምራሉ።

ለቻን ውድድር ማጣርያ ዛሬ አመሻሽ ወደ መቐለ በማቅናት በነገው ዕለት ዝግጅታቸው የሚጀምሩት ዋልያዎቹ ለ24 ተጫዋቾች ጥሪ ሲያደርጉ ከባለፈው ሳምንት የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ስብስብ ሰባት ለውጦች አድርገው ተመልሰዋል በዚህም ቀደም ብለን ባቀረብነው ዘገባ ላይ ከተጠቀሱት አስቻለው ግርማ እና መሳይ ጳውሎስ በተጨማሪ የባህር ዳር ከተማው አዲስ ፈራሚ ፍፁም ዓለሙ እና የመከላከያው ፍቃዱ ዓለሙ አዲስ የተጨመሩ ተጫዋቾች ሆነዋል።

ወደ ዝግጅት የሚያመሩ ተጫዋቾች

ግብ ጠባቂዎች (3)፡ ጀማል ጣሰው፣ ለዓለም ብርሀኑ፣ ምንተስኖት አሎ

ተከላካዮች (8) ፡ አህመድ ረሺድ፣ አስቻለው ታመነ፣ ያሬድ ባዬ፣ አንተነህ ተስፋዬ፣ ረመዳን የሱፍ፣ ደስታ ደሙ፣ ጌቱ ኃይለማርያም፣ መሳይ ጳውሎስ

አማካዮች (7): ከነዓን ማርክነህ፣ ዮናስ በርታ፣ ሀይደር ሸረፋ፣ ፉአድ ፈረጃ፣ ፍፁም ዓለሙ፣ አማኑኤል ዮሀንስ፣ ሱራፌል ዳኛቸው

አጥቂዎች (6)፡ አስቻለው ግርማ፣ ሙጂብ ቃሲም፣ አማኑኤል ገ/ሚካኤል፣ መስፍን ታፈሰ፣ አዲስ ግደይ፣ ፍቃዱ ዓለሙ


© ሶከር ኢትዮጵያ