መከላከያ ሁለት ተጫዋቾችን አስፈረመ


በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እንደሚቆይ ማረጋገጫ ያገኘው መከላከያ ዛሬ ሁለት ተጫዋቾችን በማስፈረም የአዲስ ተጫዋቾችን ቁጥር አስር አድርሷል።

አስቀድሞ ከሙገር ተስፋ ቡድን እስከ ዋናው ቡድን በኋላም በደደቢት፣ በሀዋሳ ከተማ፣ ሲዳማ ቡና እና በድሬዳዋ ከተማ ጥሩ ጊዜያት ያሳለፈውና በተለያዩ የተከላካይ ስፍራ ሚናዎች መጫወት የሚችለው ዘነበ ከበደ ለሁለት ዓመት በመከላከያ የሚያቆየውን ውል ፈርሟል።

በወላይታ ድቻ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና ደቡብ ፖሊስ ቆይታ ያደረገው የመስመር ተከላካይ እና የመስመር አጥቂ በመሆን መጫወት የሚችለው አናጋው ባደግ ሌላው ለሁለት ዓመት ለመከላከያ ለመጫወት የተስማማ ተጫዋች ሆኗል።

በዝውውሩ የነቃ ተሳትፎ እያደረገ ለሚገኘው መከላከያ የሁለቱ ተጫዋቾች መቀላቀል የአሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራውን ቡድን በተለያዩ ቦታዎች የሚያጫውቷቸውን ተጫዋቾችን አማራጭ ያሰፋል ተብሎ ይገመታል።

ቡድኑ በቀጣይ ቀናት የአንድ ተጫዋችን ዝውውር ካጠናቀቀ በኃላ ቡድኑ ሙሉ ለሙሉ ትኩረቱን ዝግጅት ላይ በማድግ ወደ ቢሾፍቱ ከተማ እንደሚያቀና ሰምተናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ