የቀድሞ የኢትዮጵያ ቡና አጥቂ የሩዋንዳውን ክለብ ተቀላቅሏል

በ2011 የውድድር ዘመን አጋማሽ ኢትዮጵያ ቡናን ከተቀላቀለ በኋላ መልካም እንቅስቃሴን ሲያደርግ የነበረው የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ ሁሴን ሻባኒ ለሩዋንዳው ክለብ በጌሴራን ተቀላቅሏል።

የደቡብ አፍሪካውን ክለብ ባሮካን በመልቀቅ ኢትዮጵያ ቡናን ተቀላቅሎ የነበረው የ29 ዓመቱ ቡሩንዲያዊ በቡናማዎቹ መለያ በግሉ መልካም እንቅስቃሴን ማድረግ የቻለ ሲሆን በአፍሪካ ዋንጫ ላይም ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር ወደ ግብፅ ማምራቱ የሚታወስ ነው። ተጫዋቹ በኢትዮጵያ ቡና ቀሪ የውል ጊዜ ቢቀረውም በጋራ ስምምነት ክለቡን ለቆ ወደ ሩዋንዳ ሊግ አምርቶ ለበጌሴራ የአንድ ዓመት ውል ፈርሟል።

በሀገሩ ክለብ ፍላምቢው እና ቪታ’ሎ የተጫወተው ፈጣኑ ተጫዋች ከዚህ ቀደም በሩዋንዳ ለአማጋጁ መጫወት የቻለ ሲሆን በድጋሚ ወደ ሩዋንዳ የሚመልሰውን ዝውውር አድርጓል።


© ሶከር ኢትዮጵያ