አስቻለው ታመነ በቅዱስ ጊዮርጊስ ይቆያል

በክረምቱ ከወልቂጤ ጋር ስሙ ሲያያዝ የነበረው ተከላካዩ አስቻለው ታመነ በቅዱስ ጊዮርጊስ ውሉን አራዝሟል፡፡

ተጫዋቹ ዘንድሮ በፈረሰኞቹ ቤት የነበረው ውል በመጠናቀቁ ክለቡን በመልቀቅ ወደ ወልቂጤ ያመራል የሚሉ ጭምጭምታዎች ቢኖሩም በድጋሚ ውሉን በማራዘም ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት በቅዱስ ጊዮርጊስ ቆይታን የሚያደርግ ይሆናል፡፡

ከዲላ ከተማ የእግር ኳስ ህይወቱን የጀመረው የመሐል ተከላካዩ ደደቢትን ለቆ በ2007 ክረምት ቅዱስ ጊዮርጊስን ከተቀላቀለ በኋላ ወጥ አቋሙን በማሳየት ሁለት ጊዜ የፕሪምየር ሊግ ኮከብ ተጫዋች ከመሆኑ በተጨማሪ በብሔራዊ ቡድኑም በመደበኛነት እየተጫወተ ይገኛል።


© ሶከር ኢትዮጵያ