ዋልያዎቹ በመቐለ የመጀመርያ ልምምዳቸውን አከናውነዋል

በትናንትናው ዕለት አመሻሽ መቐለ የገቡት ዋልያዎቹ ዛሬ ጠዋት ልምምድ ጀምረዋል።

ከሩዋንዳ ጋር ላለባቸውው የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) ማጣርያ ዝግጅት 24 ተጫዋቾችን ይፋ ያደረጉት አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ ዛሬ ጠዋት በትግራይ ስታድየም የመጀመርያ ልምምድ አከናውነዋል። 2:00 ላይ በመጀመረው ልምምድ በዛሬው ዕለት የሰርግ ስነ-ስርዓቱን ከሚያከናውነው የፋሲል ከነማው አምበል ያሬድ ባየህ ውጭ ሙሉ ተጫዋቾች በልምምዱ ተካፍለዋል። ያሬድም ከቀናት በኋላ ብሄራዊ ቡድኑ እንደሚቀላቀል ለማወቅ ተችሏል። ጉዳት ላይ የነበሩት አማኑኤል ዮሐንስ እና ምንተስኖት አሎም በጥሩ ጤንነት ሙሉ ልምምዳቸው ሰርተዋል።

ዋልያዎቹ ወደ ከተማዋ ሲገቡ በመቐለ 70 እንደርታ ደጋፊዎች እና በትግራይ እግር ኳስ ፌደሬሽን አመራሮች አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን ማረፍያቸውንም አክሱም ሆቴል አድርገዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ