ደቡብ ፖሊስ የመጀመሪያ ተጫዋቹን አስፈረመ

አሰልጣኝ ተመስገን ዳናን በዋና አሰልጣኝነት የቀጠረው ደቡብ ፖሊስ የመጀመሪያ ተጫዋች በማድረግ ዘላለም ታደለን አስፈረመ፡፡

በርካታ ወጣት ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ በአዲስ መልክ እንደሚያመጣ የሚጠበቀው ደቡብ ፖሊስ በአንድ ዓመት ውል ነው የመሀል የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹን ያስፈረመው፡፡ ዘላለም ከሀዋሳ ከተማ የታዳጊ ቡድን እስከ ዋናው ድረስ ከዚያም በወላይታ ድቻ፣ ሲዳማ ቡና እና ሀድያ ሆሳዕና ተጫውቶ ያሳለፈ ሲሆን በ2011 ወደ ፕሪምየር ሊግ ባደገው ወልቂጤ ከተማ አሳልፏል።

በፎርማት ለውጡ ምክንያት በፕሪምየር ሊጉ መሰንበቱን ያረጋገጠው ደቡብ ፖሊስ ትላንት በይፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ተመስገን ዳናን የክለቡ አዲስ አሰልጣኝ አድርጎ መቅጠሩ ይታወሳል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ