ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሊሰጡ ነው


በፌዴሬሽኑ አሰራር ክፉኛ መማረራቸውን በተለያዩ አጋጣሚዎች እየገለፁ የሚገኙት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና በወቅታዊ ጉዳይ ዙርያ በጋራ በመሆን በሸራተን ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ አዘጋጁ።

ከሰሞኑን ፌዴሬሽኑ አዳዲስ ይዟቸው የመጣቸው የሊግ አደረጃጀት፣ የሊግ ኩባንያ ምስረታ እና ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮችን አስመልክቶ በተዘጋጀው በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ ክለቦቹ ፌዴሬሽኑ እየሄደባቸው ባሉ አካሄዶች ዙርያ ያላቸውን አቋም ለሚዲያው ይፋ የሚያደርጉ ሲሆን ከዚህ ባሻገር በአንድ ባለሙያ ጥናታዊ ፁሁፍ እንደሚቀርብ ሰምተናል።

ጋዜጣዊ መግለጫውም ቅዳሜ መስከረም 10 ቀን 2011 በ08:00 በሸራተን ሆቴል እንደሆነ ሰምተናል።

* የቀንና የሰዓት ለውጥ ካለ ማስተካከያ የምናቀርብ ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ